ቤተማርያም
Betemariam
ማርያም ድንግል
Saturday, April 11, 2020
ይህ ድረ ገጽ የኢ ኦ ተ ቤተክርስቲያን ግጻዌ የያዘ ሲሆን
የቤተ ክርስቲያንዋን ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጉዳዮች
የሚስተናገዱበት ነው
Saturday, April 11, 2020
የእመቤታን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም
ፍቅሯ ቸርነቷ አይለየን
አገር
አገር በታሪክ በቋንቋ በሃይማኖት በልማድ በተስፋ በደስታና በመከራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ የሆነ ሕዝብ
የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው።
አገር ማለት አያት ቅድም አያት ተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግሥትየሚጠቅም
ሥራ ሠርተው እድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻቸውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው
በመወለድ እትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋር ስለሚዋሃድ የአገሩ አፈር ሕዝቡ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው።
እግዚአብሔር ከምድሯ ፍሬ ሕይወት እንዲገኝባት በማድረጉ አገር እያጠባች የምታሳድግ ፍሬዋ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆነች እናት ማለት ነው።ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለማደግ አባቶች በሕይወትና በሞት
የሠሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ በስደት ሲሆኑ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው።
አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሐብት በመሆኑ ድኽነትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ የአደራ ገንዘብ ነው።
ከታሪክና ምሳሌ 3ኛ መጽሐፍ