ቤተማርያም
Betemariam
ማርያም ድንግል
Saturday, April 11, 2020
ይህ ድረ ገጽ የኢ ኦ ተ ቤተክርስቲያን ግጻዌ የያዘ ሲሆን
የቤተ ክርስቲያንዋን ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጉዳዮች
የሚስተናገዱበት ነው

Saturday, April 11, 2020
የእመቤታን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም
ፍቅሯ ቸርነቷ አይለየን



 
አብርሐምና ሶሥቱ እንግዶች
  
አብርሐም ትሁት ሰውን የሚወድ ሰውን የሚያከብር  ነው ።አብርሐም ሽማግሌ ነው  ሚስቱ ሳራ ትባላለች ልጅ አልነበራቸውም። አብርሐም ለእግዚአብሔር በመታዘዙ  እግዚአብሔርም ንብረቱንና ሐብቱን ባርኮለት በጣም ሐብታም ነው። አግዚአሔርም ዘርህን አብዛዋለሁ ልጅም ትወልዳለህ ብሎት ነበር አብርሃም ግን በጣም አርጅቶ ነበር።
   
አብርሐም እንግዳ ከመውደዱ የተነሳ እንግዳ ካልመጣ ምግብ አይበላም ነበር  ።ምግብ የሚመገበው ከሰው ጋር ነው በየጊዜው ስዎች ከርሱ ጋር ለመመገብ አቤቱ ይመጣሉ።
በዚህ መልካም ሥራው  ሰይጣን ቀናበትና አብርሐም ደግ ሰው ስልሆነ  ክፉ ሊያደርገው 
አብርሐምን ሰው ሁሉ ስለሚወደው አንዲጠላ ለማድረግ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ሊያለየየው ተንኮል ፈለግ ካዛ አንድ ቀን  በአብርሐም  የቀናው ሰይጣን በሰው መልክ ተገልጦ ራሱን አንደተመታ አድርጎ ደሙን እያፈሰሰ ወደ አብርሐም ቤት ወደሚወስደው መንትያ(መንትያ መንገድ ላይ ብዙ ሰው ይገኛል) መንግገድ   ላይ ተኝቶ  ወደ  አብርሐም ቤት የሚሄዱትን እንግዶች ሁሉ እንዲህ ብሎ ነገራቸው የዱሮው አብርሐም አይምሰላችሁ  እኔም እንደ ድሮው መስሎኝ እቤቱ ብሄድ  እንዲህ  ደብድቦኝ ደሜን አፍስሶ ለቀቀኝ  እናንተንም ደማችሁን አንዳያፈሰው እያለ ወደ አብርሐም ቤት እንዳይሄዱ  አሰፈራራቸው።አብርሐምን የሚጎበኙት  ወዳጆቹ  ሁሉ እቤቱ ከሄዱ ደማቸው ስለሚፈስ እና ስለፈሩ ቀሩ። አብርሐምም የሰይጣንን ተንኮል ሳያውቅ ሦስት ቀን ሙሉ ምንም ምግብ ሳይበላ እየተራበ ጠበቀ።
ታዲያ እግዚአብሔር  ይህንን ስለአየ አንድ ነገር አደረገ።በሦስተኛው ቀን አብርሐም ከድንኳን ደጃፍ ባለችው  ዛፍ ሥር ተቀምጦ   አንድ ሰው አንክዋን  አብሮኝ የሚበላ  ከመጣ ብሎ እየጠበቀ ሳለ  በሰይጣም ተንኮል ያልተሸነፈውን  አብርሐምን   ያየ እግዚአብሔር  የሠይጣንን ተንኮል ሊሽር ለአብርሐም ደግሞ በረከትን ሊሰጥ በመምሬ ዛፍ ሥር በሦስትነቱ ተገለጠለት። ሶስት ስዎች አብርሐም መጡ ።አብርሐም በጣም ደስ አለው ።ግቡ ምግብ ይዘጋጅ አብረን እንብላ ።እግራችሁን ታጠቡ ብሎ ውኃ አቅርቦ አግራቸውን አጠበ ።አሱ ሳያስብው ለካ በእንግድነት ያስተናገዳቸው ስዎች አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ነበሩ (ስላሴ) እግዚአብሔር እራሱ ነበር።
ልጆች እንደ አብርሐም በእምነታችን ከጸናን አምላካችን ከሰይጣን ትጠብቀናል ።አንግዳ መቀበልና ማስተናገድ አንዴት በረከት አንዳለው ተረዳችሁ

      ደጉ ሳምራዊ
   
አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ የሚባል ሐገር በእግሩ ሲሄድ ብቻውን ነበር። አንድ ጫካ ሲደር   ሶስት ወንበዴዎች ወይንም ሽፍቶች  አገኙት እነርሱም ደግሞ ያለውን ገንዘብና ንብረት ወሰዱበት ሊሞት ትንሽ ሲቀረው ደም በደም አድርገው ትተውት ሄዱ። ሰውየው አርዱኝ ልሞት ነው እያለ መንገደኛውን ሁሉ ይለምን ነበር።
   
ድንገትም አንድ የአይሁድ ካህን የአግዚአብሔርን ሕግ የሚጠብቅ  በዚያ መንገድ ሲሄድ አይቶትም ምንም አርዳታ ሳያደርግለት  ገለል ብሎ አለፈ። ቆይቶ ቆይቶ ደግሞ አንድ ሌላ ሌዋዊ የሆነ ሰው  ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት አርሱም   ምንም ሳይረዳው  አለፈ።
   
ከዛ ልጆች አንድ  ሰማራ ከምትባል ሐገር የመጣ  ሳምራዊ  ሰው   ወድቆ መንገድ ዳር ደም በደም ወደ ሆነው ሰው  መጣ አይቶትም አዘነለት ። ቀርቦትም ዘይትና የወይን ጠጅ በቁስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው። በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች መቀበያ(ሆቴል) ወሰደው ጠበቀውም ተንከባከበውም 
በማግስቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለሆቴሉ  ሰጠና ጠብቀው ከዚህም በላይ ያለውን ወጪ ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ ብሎ አደራ ሰጥቶት ሄደ።
ልጆች በህወታችን ሁሉ ሰውን መጠየፍ አንደሌለብን ሁሉንም ሰው አኩል ማየት እንዳለበን በሽተኛም ቢሆን የቆሰለም ቢሆን የተራበም ቢሆን አርዳታ ማድረግ  አግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል
ልጆች  በሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለቆሰለው ሠው ባልንጀራ  ጓደኛ  የሆነው ማንኛው ይመስላችኋል?   
ካህኑሌዋዊው ? ወይስ ሳምራዊው ?
ባልንጀራህን ውደድ የሚለው ትእዛዝ  በተግባር የምንፈጽመው   ይህን ስናደርግ ነው
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!!!
              አይጥና የድመት ሰርግ
በአንድ ወቅት አይጦች ሁሉ ተሰባስበው ችግራቸውን እየተወያዩ ሳለአንደኛው ምን ብናደርግ ይሻለናል? ድመቶች አየያዙ እየበሉ እየጨረሱ ነው! ”አለ፡፡
ሌሎቹም አይጦችአይጦችን በድመቶች ከመበላት የሚያድነው ብቸኛው መንገድ ከድመቶች ጋር በጋብቻ (መዛመድ)መተሳሰር ነው::” አሉ፡፡ ከአይጦቹ አንዱ አስተዋይ አይጥ እንዲህ አለ ።ድመትን አትመኑ ለማንኛውም የሰርጉ ቀን ድመት  ሊበላን ከሞከረ ለማምለጥ አንዲያመቸን ብዙ ጉድጓድ እንቆፍር አለ ለሎቹም ተስማሙ።ከዚያም  አንጋፋ አይጦችን መርጠው ለሽምግልና ወደ ድመቶች ላኳቸው፡፡
ሽማግሌ አይጦቹምእባካችሁ ጠላትነት ይቅርብን:: ፀባችንን አቁመን በጋብቻ እንተሳሰር፡፡ብለው ድመቶችን ጠየቁ፡፡ከድመቶቹም አንዱይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለ::አይጦቹምአንዲቷን ሴት አይጣችንን ለአንዱ ወንድ ድመታችሁ ሚስት ትሆነው ዘንድ እንሰጣችኋለን፡፡አሉ፡፡ በዚህም ተስማምተው የሰርጉ ቀን ተቆረጠ፡፡ ሽማግሌዎቹም ወደ አይጦቹ ተመልሰው ስለሆነው ነገር ሁሉ ሲነግሯቸው አይጦቹ በጣም ተደሰቱ፡፡በሰርጉም እለት ድመቶቹ ወደ አይጦቹ ቤት እየጨፈሩ መጡ፡፡ እየጨፈሩም እያለ ጭራዎቻቸው ቀጥ ብለው ቆመው ነበር፡፡ አይጦቹም በሩቅ በጥንቃቄ ያዩአቸው ነበር፡፡ ድመቶቹ እንዲህ እያሉ ይዘፍኑ ነበር፡፡ 
ቤቷ እዚያ ላይ ነው አንገቷም እንደ ለጋ ዛፍ ነው፡፡እያሉ እየዘፈኑ ሲመጡ አንዱ አይጥ ይፈራናእባካችሁ ወደ ቤት ውስጥ ገብተን እዚያ ሆነን እንያቸው፡፡አለ:: ሌላዎቹ አይጦችለምን? ሰርግ አይደለም እንዴ?” ቢሉም አንዳንዶቹ ወደቤት በመግባቱ ስለተስማሙ ወደ ቤት ውስጥ ሲገቡ የቀሩቱ ውጪ ሆነው ሙሽራውን ይጠባበቁ ጀመር፡፡ ድመቶቹ እየጨፈሩ ደርሰው አይጦቹን ዘለው ሊይዝዋቸው ሲሉ እየሮጡ ጉድጓድ ገቡ፡፡ እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል አሉ።
ልጆች ከዚህ የምንማረው ቁም ነገር
ሁልጊዜ አንድን ነገር በትክክል ይሆናል ብሎ ማሰብ በቂ አንዳይደለ አና ባይሆንስ ባይስካስ ብሎ አንደ  አማራጭ  ሌላ መንገድ አየጋጅቶ  መጠበቅ አንደሚገባ አንማራለን

            ውሻና አህያ

 
በአንድ ወቅት የአንድ ሰው ንብረት የነበሩ አንድ ውሻና አንዲት አህያ ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ውሻው አህያዋን እንዲህ አላት፡፡ሌሊት ሌሊት እየጮህኩ የጌታዬን ንብረት መጠበቅ ሰልችቶኛል፡፡አህያውም እንዲህ ብላ አማረረችእኔም ጌታዬ ወደ ገበያ በሄደ ቁጥር ከባድ ጭነት መሸከም ሰልችቶኛል፡፡ ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?”በመጨረሻም ቤታቸውን ጥለው ለመጥፋት ተስማምተው ተሰደዱ፡፡ እየተጓዙም ሣለ በጣም ለምለምና ውሃ ያለው ሜዳ አጠገብ ደረሱ፡፡ አህያዋ የምትበላውና የምትጠጣው ነገር አግኝታ ስትጠግብ ውሻው ምንም አላገኘም፡፡
   
እናም አህያዋ ከጠገበች በኋላአሁን ማናፋት አለብኝ::” አለች፡፡ ውሻውም አህያዋ እንዳታናፋ እንዲህ ብሎ መከራትካናፋሽ የመጀመሪያው ድምፅ ጅቡን ይቀሰቅሰዋል፣ ሁለተኛውም ድምጽ ያለንበትን ቦታ ይጠቁመዋል፣ በሶስተኛውም አንቺን ይበላሻል፡፡
አህያዋም ምክሩን ችላ ብላ አናፋች፡፡ ጅቡም ድምጿን ሰምቶ በመምጣት አህያዋን መብላት ጀመረ፡፡
   
ጅቡም አህያዋን እየበላ ሳለ ውሻው ዝም ብሎ ይመለከት ነበር። ጅቡም ርቦት ስለነበር ውሻውን አላስተዋለውም ።ድንገት ቀና ሲል አየውና አንተ ደግሞ እዚህ ምን ትሠራለህ  ብሎ ጠየቀው ውሻውም  አንተ እንድትበላ ሥጋውን እየቆረጥሁ  ላቀርብልህ ነው የመጣሁት አለው ።ጅቡም በል እኔ ቁጭ አላለሁ አንተ አቅርብልኝ አለው።  ሥጋውን እየቆረጠ ያቀርብለት ነበር፡፡  ውሻው ባጣም ርቦት ስለነበር ምጀመሪያ ያገኘው ልብዋን በላው።  ታዲያ ጅቡ ውሻውንየአህያዋን ልብ ስጠኝ::” ቢለው ውሻውአህያዋ ልብ የላትም፡፡ ልብ ቢኖራትማ  ኖሮ  እዚህ  በጨለማ ባልመጣች ብሎም  ባላናፋች ነበር፡፡አለው ይባላል፡፡

ከአህያዋ ዐመል የምንማረው
 
እህያዋ ስትጠግብ የመጮህ  አመል አለባት ። አመል ካለብን መተው አንዳለብን  አለበለዚያ  አመል ያወጣል ከመሃል አንዲሉ እንደሚጎዳን እንማራለን

              ለሰው ሞት አነሰው
     
በአንድ ወቅት ነብር መግደል የፈለጉ  ሰዎች ነበሩ፡፡  ባጫካም አግኝተውትም  ሊገድሉት ሲሉ ነብሩም አይቷቸው ሲሮጥ በመንገዱ ላይ አንድ ገበሬ አገኘ፡፡
ገበሬውም እርሻውን እያረሰ  ጊዜውም ዘር የሚዘራበት  ስለሆነ በስልቻ ወይንም በከረጢት ዘር  ዛፍ ሥር አድርጎ ነበር እየሮጠ ገበሬው አዛረሰ በማሳው ደረሰ
ነብሩምየዘሩን ከረጢት አቀብለኝና ከአዳኞቹ አድነኝ እባክህ፡፡”  ብሎ ገበሬውን ለመነው፡፡ ገበሬውም እሺ ብሎ  ነብሩን በስልቻ አድርጎ አፉን አሰረውና  ዛፉ ስር አስቀመጠው የዘር መያዣው ውስጥ ደበቀው፡፡
     
ሁለቱም አዳኞች ገበሬው ሲደርሱ ቆም ብለውአንድ ነብር አይተሃልአሉት፡፡ገበሬውምአዎ በዚህ በኩል ሄዷል፡፡አላቸው፡፡ አዳኞቹም ሩጫቸውን ቀጠሉ፡፡በዚህ ጊዜ ገበሬው ነብሩንነብር ሆይ አዳኞቹ ስለሄዱ በል ሂድ፡፡አለው፡፡ነብሩ ግንወይ እገድልሃለሁ ወይም ምግብ አምጣልኝ፡፡አለው፡፡የሚዳኘን እንፈልኛ ነገሩ በችሎት ይዳኝ ትብሎ  ከእንሰሳት ዳኛ ሲፈልጉ  ቀበሮ አንድትዳኛቸው ነብርና ገበሬ ተስማሙ
    
ከዚያም ወደ ቀበሮ ሄዶ ገበሬውይህንን ነብር ከሞት አዳንኩት፤ ሆኖም አሁን ሊበላኝ ይፈልጋል፡፡አላት፡፡ላስብበት ብላ ለሌላ  ቀን ቀጠሮ ሰጠቻቸው ።ከቀጠሮው በፊት  ገበሬው ወደ ቀበሮ ሄዶ  ከዚህ  ነብር ከመበላት ካዳንሽኝ የበግ ግልገል አመጣልሻለሁ ብሎ  አላት። አስዋም እሺ ግድ የለም አድንሃለሁ ብላ ተስማሙ።የፍርዱ ቀን ደረሰ እና  ቀበሮም በዳኝነት ተሰየመች ሌሎች ተመልካቾች ጥሪ የተደረገላቸው አንሣትም ተሰበሰቡ
ቀበሮዋምእንዴት ነው ያዳንከው ስትለው  ስለ  ስለተደበቀበት የዘር ስልቻ ከረጢት  ነገራት፡፡
     
በሉ ለመፍረድ አንዲመቸኝ ነገሩን በተግባር አሳዩኝ ብላ አዘዘች    ገበሬው ነብሩን እንደገና ዘር ባመጣበት ስልቻ ጨመረው ፡፡ በዚህ ጊዜ ቀበሮዋ ገበሬውንበል አሁን አጥብቀህ እሰረው፡፡ስትለው ገበሬው ነብሩን በደንብ አድርጎ ካሰረው በኋላ ቀበሮዋአሁን ነብር  በስልቻ ከምድር  ከእጅ በትር   አለችው  ገበሬውም ነብሩን ደብድቦ ገደለው፡፡
    
ቀበሮና ገበሬ በተስማሙት መሰረት በበግ ጠቦት ፋንታ በውሻ ሊያስበላት ትልቅ ውሻ ይዞ መጣቀበሮዋም ከሩቁ  አይታ ስለነበር  “ለሰው ሞት አነሳው፡፡አለች ይባላል፡፡
ልጆች ከዚህ የምንማረው
   
ለኛ ጥሩ ያደረገልንን ሰው ማመስገን ኢንጂ በተቃራኒው መጉዳት እንደሌለብን አንማራለን
                     ዛፎቹ  
ከዕለታት አንድ ቀን በዓለም ዙሪያ ያሉ ዛፎች ተሰባስበው ስለ ችግሮቻቸው ይወያዩ ነበር፡፡
ከመሃከላቸውም አንዱ እንዲህ አለየእኛ ትልቁ ችግር የደን መመንጠር ነው፡፡ ይህም ድርጊት የሚፈፅምብን መጥረቢያ  በተባለ መሣሪያ ነው፡፡ ስለዚህ ጠላታችን የሆነውን መጥረቢያን ማጥፋት አለብን፡፡
   
ብዙዎቹም በዚህ ሃሳብ ዙሪያ አስተያየት በመስጠት መጥረቢያ ነው የሁልጊዜ የስቃያችን ምንጭ ይቆርጠንና ቢያሻው ለማገዶ አሊያም ለቤት ዕቃ መሥሪያ፤ እረ ምኑ ቅጡ! ስለዚህ አንድ መላ ፈልገን ይህንን ጠላታችንን ማጥፋት አለብን፡፡ ብለው መከሩ፡፡
አንድ  ዛፍም እጁን አውጥቶጠላታችን ግን መጥረቢያ አይመስለኝም፡፡አለ፡፡
በዚህን ጊዜ ሁሉም ዛፎች ወደርሱ ዞረው እንዴ! ምን ማለትህ ነው? እሱ ካልሆነ ታዲያ ማን ሊሆን ይችላል?” ብለው ጮኹበት፡፡
   
ዛፉም ንግግሩን እንዲህ ሲል ቀጠለአያችሁ እኔ ከልቤ ነው የምላችሁ ጠላታችን መጥረቢያ አይደለም እኛው ራሳችን ነን፡፡ ሁላችንም መጣመም ትተን ቀጥ ብለን ብናድግ ኖሮ መጥረቢያ አጀታ አይኖረውም፤ እኛም ከመቆረጥ  እንድን ነበር፡፡
ስለዚህ ከዚህ በኋላ ሁላችንም ሳንጣመም ቀጥ ብለን በማደግ መጥረቢያውን እጀታ መሳሳት አለብን፡፡ በዚህም ጊዜ ሁሉም ዛፎች አጨበጨቡለት

ልጆች ከዚህ የምንማረው
   
ሁል ጊዜ ከሰው ጋር አብረን ስንኖር ቀና  አመለካከት ያለን መሆን አንዳለበት። በሌላ ሰው ክፉ የሚያመጣ ነገር አለመስራት።