ቤተማርያም
Betemariam
ማርያም ድንግል
Saturday, April 11, 2020
ይህ ድረ ገጽ የኢ ኦ ተ ቤተክርስቲያን ግጻዌ የያዘ ሲሆን
የቤተ ክርስቲያንዋን ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጉዳዮች
የሚስተናገዱበት ነው
Saturday, April 11, 2020
የእመቤታን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም
ፍቅሯ ቸርነቷ አይለየን
ባሕረ ሐሳብ ከሁለት የግዕዝ ቃላት የተገኘ ሲሆን
ባሕር = ዘመን
ሀሳብ = ቁጥር ማለት ነው።
ስለዚህ የዘመን ቁጥር ማለት ደግሞ የዘመን ስሌት የዘመን ቀመር ይሆናልየኛ ቤተክርስቲያን ዘመን አቆጣጠር የሚጀምርው ከስነ
ፍጥረት ነው (ማክሰኞ ቀን) የአውሮፓውያን ደግሞ ከክርስቶስ ልደት ይጀምራል ።የኛ ቤተክርስቲያን የጨረቃንም የዘመን
አቆጣጠር ስትጠቀም በተለይ በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ለእስላሙም ሳይቀር የጨረቃ ዘመን አቆጣተር ከፍተኛ ፋይዳ አለው ። ለምሳሌ
ዘር ለመዝራት ለመትከል ወይንም ዛፍ ለመቁረጥ የጨረቃንውና ሌሊቱን በመቁጠር በዚህ ቀን መልካም ነው ይላሉ። ይህ አውቀት
ታዲያ ሳይንስ ነው ።ምርምር ቢደረግበት ከሳይንሱ ጋር አብሮ ቢዳብር መልካም ነበር ። አውሮፓያን ገበሬዎችም አንዲሁ የባህላዊውን
የዘር ወይንም ለሎች ጥቅሞችን በሳይንስ በመደገፍ ጥሩ ምርት ያገኛሉ።ከዚህ ቀጥሎ በካላንደሩ ባህረ ሃሳብን ወደ ኮምፒውተር አንዴት
ፕሮግራም (CODE) አንዳደረጉት በመጠኑ ላማሳየት እሞክራለሁ
ዑደቶች
ዐውደ ዕለት – ከእሑድ እስከ ቅዳሜ ያሉት 7 ዕለታት ሲሆኑ ወራትን ያስገኛሉ፡፡
getDay() የሳምንቱን ቁጥር ይሰጠናል (0-6)
0= እሁድ ፣1 =ሰኞ ፣ 2=ማክሰኞ፣ 3=ረቡእ፣ 4=
ሐሙስ ፣ 5= ዓርብ ፣6=ቅዳሜ
ዐውደ ወርኅ – በፀሐይ 30 ዕለታት፣ በጨረቃ 29 ወይም
30 ዕለታት ናቸው፤ እነዚህ ወራቶች ዓመትን ያስገኛሉ፡፡
getMonth() Get the month as a number (0-11) የፈረንጆቹን ወር ይሰጠናል
getDate() Get the day as a number (1-31) የወሩ ቀን ስንት አንደሆነ ይሰጠናል
ይህ የቀን መቁጠሪያ በበለጠ የተዘጋጀው የፈረንጆቹን ካሌንደር የዕለት ተዕለት ተጠቃሚ ለሆኑ ወገኖች ሲሆን በአንዷ ሳጥን ውስጥ የፈርንጆቹ ቀን እንደ መሪ ተደርጎ ተወስዷል ቀጥሎ በካላንደሩ አንዱ ሳጥን ወስጥ በሰማያዊ ቀለም ለምሣሌ 12/16 የሚታየው ሌሊት/ጨረቃ ነው። ከታች ደግሞ በአረጓዴቀለም
ለምሣሌ ፳፩/21 የሚታየው የኢትዮጵያ ካሌንደር ቀን በግዕዝና በላቲን ፊደል ነው።በእያንዳንዱ ቀን ላይ በማውስ ክሊክ ሲየደርጉ ከግጻዌ የዕለቱን ምንባብና ምስባክ አንዲሁም የሚከበሩ ዘመላእክት የጻድቃን የሰማዕታት በዓላት ያገኛሉ። ቀስቶቹን አንድ ዓመት ወደ ፊትና ወደ ኋላ በማውስ ሲጫኑ ዓመቱ ወይንም ወሩ ይቀየራል።
በታችኛው መስኮት ደግሞ የዓመቱን አጽዋማትና በዓላትን ከባሕረ ሐሳብ ወደ ኮምፒውተር ፕሮግራም በመቀየር እንዲስራ ተድርተግዋል ቀጥሎ አንዳንድ የፕሮግራሙን ኮድ በማብራራት በማሳየት ሌሎች ፕሮግራም ወይንም ኮድ ማድረግ ለሚፈልጉ አንዲረዳ ተቀምጠዋል
ማስታወሻ
1 ራዕቢት ማለት አስከ አሁን ያሉት ጳጉሜን 6 ሲደመር ነው
2 % ማለት በብዙ የፕሮግራም ቋንቋ Mod በኛ መግደፍ መለት ነው
ለምሳሌ 44%7= 2 ይሆናል ወይንም 97%30 = 7 ነው
3 ዐውደ አበቅቴ በየ19 ዓመት የሚመጣ ሲሆን ጨረቃና ጸሐይ ጠዋት አኩል ወጥተው ማታ አኩል ይገባሉ
አበቅቴ የሚባለው መስከረም 1 ቀን ሲጀምር የጨረቃ አመታዊ እድሜዋ ነው ።
ጨረቃ የሚቀጥለውን ዓመት የምትጀምርበት ቀን ልደተ አበቅተ ይባላል።
ጨረቃ መጀመሪ ሙሉ ገጿን ይዛ ስትወጣ ተወለደች ይባላል ሠረቀ ሌሊት ( የሌሊት መውጫ ) ይባላል።
የጸሐይ ወር የሚጀምርበት ዕለት ደግሞ ሠረቀ መዓልት (የቀን መውጫ የብርሃን መጀመሪያ ጥንተ ዮን ) ይባላል።
x=etyear(yearNum); // የኢት ዮጵያን ዓመት ይሰጠናል
y=x+5500; // ዓመተ ዓለም ። ከዘፍጥረት ጀምሮ
rabit=(y-(y%4))/4 ; // ራዕቢት በ4 ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜን 6 ከዘፍጥረት ጀምሮ ተደምረው
„ % „ በብዙዎች ፕሮግራም ቋንቋ Mod መግደፍ ማለት ነው
z=y%4; // mode 4 // ውንጌላውያን የዘመኑን ወንጌላዊ ለማወቅ 5500 ዓ.ዓ ና ዓመተ ምሕረት ደምረን ለአራት በማካፈል ቀሪው 1 ከሆነ ማቴዎስ፣ 2 ከሆነ ማርቆስ፣ 3 ከሆነ ሉቃስ፣ አልቦ /ዜሮ/ ከሆነ ዮሐንስ ነው።
switch( z) {
case 0:
{
Wengelawi= "ዮሐንስ";
brake;
}
case 1:
{
Wengelawi ="ማቴዎስ";
brake;
}
case 2:
{
Wengelawi ="ማርቆስ";
brake;
}
case 3:
{
Wengelawi = "ሉቃስ";
brake;
}
}
se1=(y+rabit)%7;
መስከረም 1 ቀን የሚውልበት ቀን
wenber=(y%19)-1;
se1:- 0 ከሆነ አሁድ ፣ 1 ከሆነ ሰኞ ፣2 ከሆነ ማክሰኞ፣ 3 ከሆነ ረቡዕ፣
4 ከሆነ ሐሙስ ።5 ከሆነ ዓርብ ።6 ከሆነ ቅዳሜ።
switch( se1) {
case 0:
{
wort1="ርዕሰ ዐውደ ዓመት መስከረም ፩ ሰኞ ";
break;
}case 1:
{
wort1= "ርዕሰ ዐውደ ዓመት መስከረም ፩ ማክሰኞ " ;
break;
}
case 2:
{
wort1= "ርዕሰ ዐውደ ዓመት መስከረም ፩ ረቡዕ";
break;
}
case 3:
{
wort1 " ርዕሰ ዐውደ ዓመት መስከረም ፩ ሐሙስ ";
break;
}
case 4:
{
wort1="ርዕሰ ዐውደ ዓመት መስከረም ፩ አርብ ";
break;
}
break;
}
case 5:
{
wort1= "ርዕሰ ዐውደ ዓመት መስከረም ፩ ቅዳሜ";
break;
}
case 6:
break;
{
wort1= "ርዕሰ ዐውደ ዓመት መስከረም ፩ እሁድ";
}
if((y%19)==0)
{
wenber=18; //(0-1)
ዓመተ ዓለም ለ19 ተካፍሎ የሚገኘው ቀሪ ተረፈ ዘመን (ወንበር) ይባላል፡፡
19 ዐውደ አበቅቴ ነው
}
else{
wenber=(y%19)-1
}; // y=Amete alem
if((y%19)==1)
{
wenber=0; // abekte 30 (1-1)
metki=30;}
metki=(wenber*19)%30; //መጥቅዕን ለማግኘት ወንበር ሲባዛ በጥንተ መጥቅዕ (፲፱) ሲካፈል ለ፴ ኾኖ ቀሪው መጥቅዕ ይባላል፡፡
abekitemedeb=365-354;// የመሬት ዓመት - የጨረቃ ዓመት 365 የመረት ዑደት ሲሆን 354 ደግሞ የጨረቃ ዑደት ነው
abekite= (wenber* abekitemedeb)%30; //መጥቅዕ ከ14 ከበለጠ በዓለ መጥቅዕ በመስከረም ነው ። ይህከሆነ ደግሞ ነነዌ በጥር ይሆናል ማለት ነው ( 1 ) //መጥቅዕ ከ14 ካነሰ በዓለ ምጥቅዕ በጥቅምት ነው ። ይህ ከሆነ ደግሞ ነነዌ በየካቲት ይሆናል ማለት ነው (2)
ዐውደ አበቅቴ በየ19 ዓመት የሚመጣ ሲሆን ጨረቃና ጸሐይ ጠዋት አኩል ወጥተው ማታ አኩል ይገባሉ አበቅቴ የሚባለው መስከረም 1 ቀን ሲጀምር የጨረቃ አመታዊ እድሜዋ ነው ።
ጨረቃ የሚቀጥለውን ዐመት የምትጀምርበት ቀን ልደተ አበቅተ ይባላል።
ጨረቃ መጀመሪዛ ሙሉ ገጿን ይዛ ስትወጣ ተወለደች ይባላል ሠረቀ ሌሊት ( የሌሊት መውጫ ) ይባላል።
የጸሐይ ወር የሚጀምርበት ዕለት ደግሞ ሠረቀ መዓልት (የቀን መውጫ የብርሃን መጀመሪያ ጥንተ ዮን ) ይባላል።
if(metki>14){ // (1)
tewsak=(metki+se1)%7 ; //የእለታት ተውሳክ የሚያመለክትቱት ከመጥቅዕ አስከ ነነዌ ያሉት ቀናት በ30 ሲገደፍ ነው
if (metki+se1-1+(tew(tewsak))>30)
{
tewsak=(metki+se1)%7 ; //የእለታት ተውሳክ የሚያመለክትቱት ከመጥቅዕ አስከ ነነዌ ያሉት ቀናት በ30 ሲገደፍ ነው
flag=2; //nenewe beyekatit
var textnewe="ጾመ ነነዌ የካቲት ";
tewsak=(metki+se1)%7 ;
var textnewe="ጾመ ነነዌ በጥር ";
}
}
if(metki<14) // (2)
{
tewsak=(metki+se1+30)%7 ; //የእለታት ተውሳክ የሚያመለክትቱት ከመጥቅዕ አስከ ነነዌ ያሉት ቀናት በ30 ሲገደፍ ነው
var textnewe="ጾመ ነነዌ የካቲት ";
}
ዐዋጆች
1 ጾመ ነነዌ ከጥር ፲፯ ቀን በታች፤ ከየካቲት ፳፩ ቀን በላይ አይውልም፡፡
2 ዐቢይ ጾም ከየካቲት ፩ ቀን በታች፤ ከመጋቢት ፭ ቀን በላይ አይውልም፡፡
3 ደብረ ዘይት ከየካቲት ፳፰ ቀን በታች፤ ከሚያዝያ ፪ ቀን በላይ አይውልም፡፡
4 በዓለ ሆሣዕና ከመጋቢት ፲፱ ቀን በታች፤ ከሚያዝያ ፳፫ ቀን በላይ አይውልም፡፡
5 በዓለ ስቅለት ከመጋቢት ፳፬ ቀን በታች፤ ከሚያዝያ ፳፰ ቀን በላይ አይውልም፡፡
6 በዓለ ትንሣኤ ከመጋቢት ፳፮ ቀን በታች፤ ከሚያዝያ ፴ ቀን በላይ አይውልም፡፡
7 ርክበ ካህናት ከሚያዝያ ፳ ቀን በታች፤ ከግንቦት ፳፬ ቀን በላይ አይውልም፡፡
8 በዓለ ዕርገት ከግንቦት ፭ ቀን በታች፤ ከሰኔ ፲፱ ቀን በላይ አይውልም፡፡
9 ጾመ ሐዋርያት ከግንቦት ፲፮ ቀን በታች፤ ከሰኔ ፳ ቀን በላይ አይውልም፡፡
10 ጾመ ድኅነት ከግንቦት ፲፰ ቀን በታች፤ ከሰኔ ፳፪ ቀን በላይ አይውልም፡፡
ሁል ጊዜ እነዚ ባዓላት የሚውሉት ደግሞ አንደሚከተለው ነው
ጾመ ነነዌ፣ ዐቢይ ጾም እና ጾመ ሐዋርያት – ሰኞ፡፡
ደብረ ዘይት፣ ሆሣዕና፣ ትንሣኤ እና ጰራቅሊጦስ – እሑድ፡፡
ስቅለት – ዓርብ፡፡
ርክበ ካህናት እና ጾመ ድኅነት – ረቡዕ፡፡
ዕርገት – ሐሙስ
ተጨማሪ
የዓመት ክፍሎች፡- መጸው ወይንም መኸር ፣ በጋ ወይንም ሃጋይ ፣ ፀደይ ወይንም በልግ እና ክረምት ወይንም አፍላግ ጠል መብረቅ ደመና ናቸው፡፡
፩ ከመስከረም ፳፮ እስከ ታኅሣሥ ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ክፍለ ዓመት መጸው ወይንም መኸርይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት ሌሊቱ ረጅም፣ ቀኑ አጭር ነው፡፡ ነፋስ የሚበዛበት ጊዜ ነው። በቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ መንፈስ ቅዱስ ይመጽእ ላእሌኪ እንዳለ።እንዳለ።በዚህ ወቅት ተዘርቶ የከረመው አዝርዕት ለዘር የሚበቃበት ሰማያት በከዋክብት፣ ምድርም በሥነ ጽጌያት የሚያሸበርቁበት ወቅት ነው። “ዘከለልኮ ለሰማይ በከዋክብት ወለምድኒ በሥነ ጽጌያት” እንዲል ቅዱስ ያሬድ።
፪ ከታኅሣሥ ፳፮ እስከ መጋቢት ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ክፍለ ዓመት በጋ ወይንም ሃጋይ ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት እኩል ነው፡፡ፀሐይ ሙቀት የሚበዛበት ጊዜ ነው። ዮሐንስ በወንጌሉ ስለ መለኮት የሚገልጽበት ስለሆነ።ምድር በፀሐይ ሐሩር የምትቃጠልበት፣ ልምላሜ የሚጠፋበት፣ አታክልቱ በአቧራ የሚሸፈኑበት ምንም ዝናም የሌለበት ወቅት ነው።
፫ ከመጋቢት ፳፮ እስከ ሰኔ ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ወቅት ፀደይ ወይንም በልግ ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት ቀኑ ይረዝማል፤ ሌሊቱ ያጥራል። የዘር ጊዜ ነው ።ማቴዎስ በወንጌሉ ዘሪ ሊዘራ ወጣ ብሎያስተምራል ።፡፡በዚህ ወቅት ምድር ትንሽ ዝናም የምታገኝበት በተወሰነ ደረጃ ልምላሜ የሚታይበት ወቅት ነው።
፬ ከሰኔ ፳፮ እስከ መስከረም ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ክረምት ወይንም አፍላግ ጠል መብረቅ ደመና ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት እኩል ነው፡ ወርሃ ማይ በመሆኑ ።ማርቆስ በወንጌሉ በጥምቀት ይጀምራል ።ክረምት ከረመ ማለት ሲሆን ምድር በዝናም የምትቆይበት ጊዜ ነው።
የኢትዮጵያ የዓመቱ ወራት ሥፍረሰዓት በቤተክርስቲያናችን
፩ መስከረ የቀኑ ርዝመት12 የሌሊቱ ርዝመት12 ሪና መአልት ሪና ሌሊት ዘመጸው (ቀኑም ሌሊቱም አኩል)
፪ጥቅምት የቀኑ ርዝመት 11 የሌሊቱ ርዝመት13
፫ ህዳር የቀኑ ርዝመት 10 የሌሊቱ ርዝመት14 መጸው ወይንም መኸር
፬ ታህሣሥ የቀኑ ርዝመት 09 የሌሊቱ ርዝመት15 ረጅሙ ሌሊት አጭሩ ቀን
፭ ጥር የቀኑ ርዝመት 10 የሌሊቱ ርዝመት14
፮ የካቲት የቀኑ ርዝመት 11 የሌሊቱ ርዝመት13 በጋ ወይንም ሃጋይ
፯ መጋቢት የቀኑ ርዝመት12 የሌሊቱ ርዝመት12 ሪና መአልት ሪና ሌሊት ዘጸደይ (ቀኑም ሌሊቱም አኩል)
፰ ሚያዝያ የቀኑ ርዝመት13 የሌሊቱ ርዝመት11
፱ ግንቦት የቀኑ ርዝመት 14 የሌሊቱ ርዝመት10 ፀደይ ወይንም በልግ
፲ ሰኔ የቀኑ ርዝመት 15 የሌሊቱ ርዝመት09 ረጅሙ ቀን ዐጭሩ ሌሊት
፲፩ ሐምሌ የቀኑ ርዝመት 14 የሌሊቱ ርዝመት10
፲፪ ነሐሴ የቀኑ ርዝመት 13 የሌሊቱ ርዝመት11 ክረምት ወይንም አፍላግ ጠል መብረቅ ደመና
አንድ ዓመት 365 ቀን ከ 6 ሰዓት ከ 2 ደቂቃ ነው ስለዚ 4ቱ ዘመናት የሚጀምሩበት ቀን መስከረም 1 ቢሆንም በሰዓት ይለያያል።
ማቴዎስ ዘመኑን ከምሽቱ ፩ ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ይፈጽማል፡፡
ማርቆስ ዘመኑን ከሌሊቱ ፯ ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከጠዋቱ ፲፪ ሰዓት ይፈጽማል፡፡
ሉቃስ ዘመኑን ከጠዋቱ ፩ ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከቀኑ ፮ ሰዓት (በቀትር) ይፈጽማል፡፡
ዮሐንስ ዘመኑን ከቀኑ ፯ ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከቀትር በኋላ ከምሽቱ ፲፪ ሰዓት ይፈጽማል፡፡
